(Read this post in English.)

በ2010 የሙዚቃ ህክምና ፕሮግራማችን ውስጥ ካካተትነው ጀምሮ FENAID ለተጠቃሚዎቹ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን ሲያዘጋጅ ኖርዋል። በዚህ ጊዜም በተቋሙ የሚገኙ ተንከባካቢዎች ሙዚቃ ለአካል ጉዳተኞች ምን ያህል ጥቅም እንዳለው መገንዘብ ችለዋል።

FENAID ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ሙሁራን ጋር በመተባበር ተጨማሪ ፍላጎት ላላቸው ህጻናት እና ትማሪዎች ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ከተቋሙ አልፎ ሙዚቃ በትምህርት ቤቶች ውስጥም ላሉ የአካል ጉዳተኞ እንክብካቤ እንዲውል ፍላጎት አለው።

በቅርብ ጊዜም ከFENAID የመጡ አጋሮቻችን ይህን የሙዚቃ አጠቃቀምን ላምስፋፋት የሚያደርጉት ጥረትን እንድንደግፍላቸው ጠይቀውናል። በአማርኛ ቋንቋ እንድ በራሪ ወረቀት አዘጋጅተን ለትምህርት ቤቶች አቅርበን ፍላጎታቸውን በማነሳሳት ስለ ሙዚቃ የበለጠ እንዲያውቁ ለማድረግም ተስማምተናል።

FENAID በኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ መልኩ የሙዚቃ አጠቃቀምን ለማስፋፋት እና ለማዳበር ሲሰራ ማየት በጣም አስደናቂ ነው።