Read this post in English.

በአዲስ አበባ ያደረግነው ሁለተኛውና የመጨረሻው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱም ፕሮጀክቶች ውስጥ ለሙዚቃ ተሳታፊዎች “ለራስን ጥብቅና መቆም” በሚል መሪ ሐሳብ ላይ የተመረኮዘ ነበር። ሥልጠናው ታካሚዎቻችን የመሪነትን ሚና እንዲጫወቱ የሚያበረታታና ባለፈው ዓመት የቀሰሙትን ዘዴዎች እንዲጠቀሙባቸው የሚጠይቅ በመሆኑ፡ ሠልጣኞቻችን በልበ-ሙሉነት ሲመሩ በማየታችን በጣም ተደስተናል።

በለቤዛ የሳይካትሪ ክሊኒክ መልካም አቀባባል ተደርጎልን ከግቢው ውጭ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት ተመልክተናል። ታካሚዎች እና ሠራተኞች ይህንን ዝግጅተ ለማሳካት አብረው ደከመዋል። የተለያዩ የሙዚቃ ዓይንቶችን ለምሳሌ አካላዊ ሙዚቃን፤ የድምጽ አጠቃቀምን፣ የሙዚቃ መሣሪያዎችን እንዲሁም ባህላዊ ውዝዋዜን ያካተተ ዝግጅት ነበር። የሙዚቃ ቡድኑን በመቀላቀላቸው ያገኙትን ትሩፋት ያካፈሉ ታካሚዎችንም ማግኘት ችለናል፡

ጭር ሲል መንፈሴ ይረበሻል። በአእምሮዬና በሀሳቤ ብዙ ዓለም እጓዛለሁ። በሙዚቃው ቡድን ውስጥ ከአእምሮዬ ውጭ
ያለው ድምፅ ያለ የመሆን ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጋል

ታካሚ፣ የለበዛ የአእምሮ ህክምና ክሊኒክ

ለቤዛ የአዕምሮ ህክምና ክሊኒክ የተሰበረውን ቦንጎ የሙዚቃ መሣሪያ ማስጠገኛ ገንዘብ በሚዩዚክ አስ ቴራፒ ኢንተርናሽናል ሥም ለመርዳት በመቻላችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ የሙዚቃ መሣሪያ በግቢው ውስጥ ላሉ ታካሚዎች የተሟላ እና አስደሳች ግልጋሎት ይሰጣል።

የFENAID ተሳታፊዎች በአስደናቂው የሙዚቃ ሰልጣኝ ጃክሰን በሚመራው የሙዚቃ እና ውዝዋዜ ቡድናቸው አማክይነት በመላ ኢትዮጵያ ስለ መማር እክል ግንዛቤ ማስጨበጥ ብቻ ሳይሆን በግለሰቦቹ የሚመራ የራሳቸውን የሙዚቃ ቡድን ለመምራት እንደሚፈልጉ ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ይህ ለህብረተሰቡ እኩልነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሚጥሩ ግለሰቦች ሌላ ትልቅ ስኬት ነው።

ሙዚቃ እወዳለሁ፣ መልእክቴን እንዳስተላልፍ ይረዳኛል፣ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደምችል፣ በመሪነት ሚና ውስጥ
መሳተፍ እንደምችል። ሰዎች ስለ እኔ የራሳቸው አመለካከት አላቸው ነገር ግን ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ።

የራስ ጠበቃ፣ FENAID

ሆስፒስ ኢትዮጵያ ሙዚቃን እንደ የቀን አገልግሎት ፕሮግራማቸው በተሳካ ሁኔታ እየተጠቀሙ ሲሆን ሙዚቃን በቤት ውስጥ እንክብካቤ ውስጥ ለመጠቀም እና በመጪዎቹ ዓመታት አዲሱን የህፃናት ሆስፒስ እንክብካቤን ለመዳሰስ ፍላጎት አላቸው። በቀጣይነት ያደረግነው ውይይትም ባህል-ተኮርና ባለፈው ዓመት ለተሰጠው ሥልጠና ከፍተኛ መነሳሳትና ጉጉት ያሳየ ነበረ።

ወደ ገፈርሳ የአእምሮ ጤና ማገገሚያ ማዕከል ያደረግነው የመጨረሻ ጉብኝታችን የሥፍራውን አመቺነት እንድንመለከትና ማስቻል ብቻ ሳይሆን የሙዚቃ ቡድኖችን በቦታው ላይ ለማከናወን የሙሉ ጊዜ ሙዚቀኛ ለመቅጠር ተስፋ አንደናደርግ አድርጎናል። ዶ/ር ገረሙ የድርጅቱን ወደ ሌሎች የእንክብካቤ ዘዴዎች የማካተት መስፋፋት ሲናገሩ፤ የሙዚቃ ቡድኖች በአሁኑ ታካሚዎቻቸው ላይ ስላላቸው በጎ ተጽእኖ እበክረው ተናግረዋል። አድናቆታቸውንም የሙዚቃ የቡድን መሪዎችን ነግረናቸው ስላከናውኑት ድንቅ ሥራ የእንኳን ደስ አለን መለዕክት አስተላልፈንላቸዋለን።

የኢትዮጵያን ባህል፣ ህዝብና ሙዚቃን በጣም ወደነዋል። የዚህ ድንቅ ፕሮጀክት አካል መሆን እና ሙዚቃ በእያንዳንዱ አጋር ድርጅቶቻችን ውስጥ ያለውን የረጅም ጊዜ በጎ ተፅእኖ ማየት እውነተኛ ክብር ነው።