Read this post in English.

በድንገተኛ በጎርፍ ምክንያት ከስኮትላንድ ወደ ደቡብ የሚሄዱ ባቡሮች ከመቋረጣቸው፤ አለስቴር ካጋጠመው የመጀመሪያ መሰናክል ሌላ፤ የተቀረው ጉዞ ቀና ነበር። ሌሊቱን በአውሮፕላን ተጉዘን አዲስ አበባ በገባን በሁለት ሰዓታት ውስጥ በኤርቢንቢ ማረፊያችን እንደደረስን ኤሪንን ለሁለተኛ ጊዜ ለማየት፤ በግንባር ቀደምትነት የመጡት ሰዎች በብዙ በፈገግታ ተቀበሉን።

ይህ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በ2018 በተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ የተካሄደውን ስልጠና ለመገምገም የተደረገ ቀጣይ ጉዞ ነው።

ባልታሰበ ሁኔታ የሹፌር ለውጥ ለማደረግ ብንገደድም ፣ የጸጥታ ኬላ ላይ ሊፍት በሰጠነው ኦሮምኛ ተናጋሪ እርዳታ ጉዟችንን ለመቀጠል ይለፍ ተሰጥቶን፤ የትራፊኩን መጨናነቅ እንድምንም አልፈን ከሁለት ሰዓት ጉዞ በኋላ በገፈርሳ ደረስን – በመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ ፕሮጀክታችን!

ከተጨናነቁ መንገዶችንና የጎዳና ተዳዳሪዎች አልፈን ወደ ወደ ገፈርሳ የአእምሮ ጤና ማገገሚያ ማዕከል ስንደርስ
ሠላማዊው የአትክልት ሥፍራውና ውብ አካባቢው፤ ከቡና ሥርዓት ጋር ተቀበሉን። በአዲስ አበባ ውስጥ ካጋጠሙን በርካታ ተቃራኒ ገጽታዎች መካከል አንዱ ነበር።

በሳምንታዊው የሙዚቃ ቡድን ለመሳተፍ የተሰበሰቡት ታማሚዎችወደ 25 የሚጠጉ ነበሩ። ክብ ሠርተው የእንኳን ደህና መጣችሁ የሚለውን ዘፍነው፤ “ጥሪ እና ምላሽ” ወደ ተሰኘው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሸጋገሩ። ብዙ ታካሚዎች ተራ እየገቡ ቡድኑን ይመሩ ነበር።

የሚቀጥለው እንቅስቃሴ ቡድኑ በሶስት ክፍሎች የተከፈለበት የ”መዘምራን” ጊዜ ነበር።፡እያንዳንዳቸው የመዘምራን ቡድን ከሌሎች የመዘምራን ቡደኖች ጋራ በተነፃፃሪነት ይዘፍኑ ነበር። እንደገናም በርካታ ሰዎች ተራ በተራ በመሳተፍና የዝማሬዎቹን ቅላጼዎች በመቀያየር፤ ወደ ኃያልና ከፍ ያለ መደምደምያ አመጡት።

ቁጥራቸው ከፍ ያለ ሐመምተኞች በየግላቸው በመዝፈን ያሳዩት ተሳትፎ፤ በባሕላዊ ዘፈንና ወዝዋዜ ከታጀበ በኋላ ሁሉም በተሳተፉበት “ሆይ ሆይ” በተሰኝው ዜማ ስንብት ተደርጓል

የሚቀጥለው እቅዳችን ሁለቱን ፕሮጀክቶች፤ ማለትም ለቤዛ የአዕምሮ ህክምና ክሊኒክንና FENAID መጎብኘት ሲሆን ከገፈርሳ የአእምሮ ጤና ማገገሚያ ማዕከል ጋር ተመሳሳይ ሳምንታዊ ቡድኖችን በማካሔእድ ላይ እንደሚገኙ ከሠራቶኞች ከወዲሁ ሪፖርት ደርሶናል። ወደ 4000 ተከታዮች ያሉት ከራስ ተሟጓቾች አንዱ በብሔራዊ ቲያትር ውስጥ የተደረገውን የዳንስ ትርኢት የሚያሳይ ቪዲዮ በቲኪቶክ በማካፈሉ የተሰማቸውን ኩራት የFENAID ሰራተኞች ራት ገልፀውልናል።እዚያ ባደረግነው የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ የመማር እክል ያለባቸው፣ ሁለት “የራስ ተሟጋቾች” ከወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች እና ሰራተኞች ጋር አብረው ነበሩ። በዚህ በእውነት ሁሉን አሳታፊ ተሞክሮ ሁሉም ሰው ድምጽ እና ቦታ በጠረጴዛው ላይ ነበረው።

የሙዚቃ ቡድኖቹ እንዴት እየሄዱ ነው የሚለውን ጥያቄ ይዘን ለቤዛ የአእምሮ ህክምና ክሊኒክ ውስጥ ስብሰባችንን ስንከፍት አንድ ሠራተኛ የተጠቀመበት የመጀመሪያ ቃል “ደስ የሚል” ነበር። ሳምንታዊ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ለማየት በሚቀጥለው ሰኞ እንመለሳለን።

አራተኛው ፕሮጀክታችን፤ ሆስፒስ ኢትዮጵያ፤ የ20 ዓመታት ሥራቸውን ያከበሩበት በሳፊሬ ሆቴል በተደረገ ዝግጅት ሲሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ለጋሾች እና የሀገር ውስጥ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተጋብዘዋል። ከታካሚዎቻቸው የአንዷ በግምባር ተገኝታ ያደረግችው ንግግርና ሌላኛዋ ደግሞ በቤቷ ሆና ስትናገር የሚያሳየው ቪዲዮ በጣም ልብ የሚነኩ አስተዋፅዖዎች ነበሩ። ይህም ላደረጉት ተጋድሎ፣ እያደረጉት ስላለው አበረታች ሥራና እንዲሁም የሕፃናት የማስታገሻ ሕክምና ወደ ፊት መራመዱን ያሳያል። ወደ ሆስፒስ ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት በሚቀጥለው ሳምንት የምንሔድ ሲሆን፤ የሙዚቃ ቡድድኖቻቸውን በዐይናችን የማየት ዕድል ባይኖረንም፤ በስላይድ አስድግፈው ከአቀረቧቸው ገለፃዎች ለመገንዘብ ችለናል።

ይህ ስብሰባ ሆስፒስ ኢትዮጵያ፣ ገፈርሳ የአእምሮ ጤና ማገገሚያ ማዕከል እና FENAID፣ ሥራቸውን በስፋት
ለማስተዋወቅ፣ ኔትወርኮችን ለመገንባት እና ሌሎች ባለሙያዎችን እና የመንግስት ድጋፍን ለማሳተፍ የሚያደርጉትን ሰፊ ሥራ እንድናሰላስል ጊዜ ሰጥቶናል።

በከታማይቷ ወስጥ ከቦታ ወደ ቦታ ብታክሲ መጓጓዝ አሰልቺና ብዙ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም፤ አሽከርካሪዎች ልብ የሚነኩ የሕይወት ገጠመኞቻቸውን ሲያክፍሉን፤ አሊያም ስለ ፖለቲካ፤ ስለ ጦርነቱ፤ ስለ እግር ኳስ እንዲሁም ስለ ሃይማኖት የሚደረጉ ውይይቶችና አስተያየቶች የጊዜው እርዝመት እንዳይታወቅን አድርርጓል። ማንቼስተርና ጋሬት ቤል በስፋት ተጥቃሾች ናቸው።