(Read this post in English)

ባለፈው ጥቅምት የሙዚቃ ቴራፒስቶቻችን ኤረን እና ኤማ ለአራት ሳምንታት ያህል ስልጠና ለመስጠት ወይም አጋሮቻችንን በአራት የተለያዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙዚቃን የመጠቀም ልማዳቸውን ለማጠናከር በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡ ይህ በአጠቃላይ 26 ተንከባካቢዎች የሰለጠኑ እና የተደገፉ ሲሆን ይህም 306 አዋቂዎች በሁሉም የእንክብካቤ ቦታዎች የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን እንዲያገኙ አድርጓል።

በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ኤማ እና ኤረን ይለቋቸው የነበሩትን እና ይሰጡዋቸው የነበሩትን የስልጠና መርሃግብሮች ያጋሩባቸውን ብሎጎች ሳታነቡ የቀራችሁ አይመስለንም፡፡ እንደሙዚቃ ቴራፒስት ያላቸው ልምድን በመጠቀም ተሳታፊዎች ልምድ ከታሳታፊዎች ጋር ተጋርተዋል፡፡

ኤረን እና ኤማ ከታካሚዎ ጋር የነበራቸው ጉብኝት ወይም ኢንተራክሽን ግሩም ነበር፡፡ የቋንቋ ገደብ ባለበት ሁኔታ ውስጥ እንኳን ይህ የእርስ በእርስ ግንኙነት እጅግ በጣም ጥሩ ነበር፡፡

በሆስፒስ ኢትዮጵያ ተሳታፊ ሰራተኛ

ኤማ እና ኤረን ሰራተኞ ሙዚቃ የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች እንዲያውቁ ካደረጉ  በኋላ ከሁሉም አገልግሎት መስጫዎች ተሳታፊዎች የተማሩትን አካፍለውናል፡፡

አዲስ የሙዚቃ ሕክምና ሥርዓቶችን እና ዘዴዎችን ተምረናል…የሙዚቃ ቴራፒ ትምህርቱን ከባህላችን እና አውድ ጋር እንዴት ማድረግ እንደምንችል መንገዶችን መርምረናል።

የሆስፒስ ኢትዮጵያ ተሳታፊ ሰራተኛ

የታካሚን ባህሪን በሙዚቃ አማካኝነት በአግባቡ ለመያዝ እና ለማስተናገድ የሚያስችሉኝን አዳዲስ ክህሎቶች ተምሬአለሁ፡፡

የለቤዛ የስነ አእምሮ ክሊኒክ ተሳታፊ ሰራተኛ

በኢትዮጵያ ካከናወናቸው እንቅስቃሴ አንዱ ተሳታፊ ሰራተኞች የራሳቸውን የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች በራስ መተማመን እና እራሳቸውን ችለው እንዲመሩ የሚያስችላቸውን ክህሎቶች ማላበስ ነበር፡፡ ከተሳታፊዎች መካከል 91% የሚሆኑን በሙዚቃ ክፍለጊዜዎቻቸው እንደኮሩ አሁን ላይ የመተማመን መንፈስ እንዳደረባቸው እና ስራቸውን ሲሰሩ የበለጠ ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ሙዚቃ ስሜታችንን ከፍ የማድረግ፣ ስሜታችንን የመግለጽ እና አዲስ ግንኙነቶችን የመፍጠር ኃይል ያለው ዓለማቀፋዊ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። በእንክብካቤ ውስጥ ባሉ ሰዎች እና በተንከባካቢዎቻቸው መካከል ግንኙነትን እና ማህበራዊ ትስስርን ሊያበረታታ ይችላል። በተጠቃሚዎቻቸው ስሜት ላይ ጉልህ ልዩነቶች ሲታዩ ፣ ይህ ሁሉ በብዙ ተሳታፊ ተንከባካቢዎች ተስተውሏል።

የተወሰኑ ድባቴ ውስጥ የነበሩ ታካሚዎች  እየደነሱ ነበር፡፡

የለቤዛ የስነ አእምሮ ክሊኒክ ተሳታፊ ሰራተኛ

መጀመሪያ አካባቢ ላይ ሳቅ ያልታየባቸው ቢሆንም አሁን ላይ ግን መሳቅ ጀምረዋል፡፡

የገፈርሳ አእምሮ ጤና ህክምና ማዕከል ተሳታፊ ሰራተኛ

ከዚህ በፊት ተናግረው የማያቁ ወጣቶች በሙዚቃ አማካኝነት ስሜታቸውን ሲገልጹ ተመልክቻለሁ፡፡

በፌናይድ ተሳታፊ ሰራተኛ

86% የሚሆኑት የህክምና አገልግሎት ሰጪዎች ተሳትፎአቸውን መጨመራቸውን፣ የመገለል ሁኔታቸውን እና ጭንቀታቸውን መቀነሱን፣ 77% የሚሆኑ ተሳታፊዎች በተጠቃዎች ስሜትን የመግለጽ፣ ከባድ ጭንቀት እና ከሰራተኛ አባላት ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ መሻሻልን ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ቡድናችን ኤሪን እና ኤማ እንደዚህ አይነት ተፅእኖ ያላቸውን ተግባራት እንድናቀርብ ለመርዳት ላደረጉት ጥረት ባለዕዳ ነን። እንዲሁም የኢትዮጵያ አጋሮቻችን ሙዚቃን ለመጠቀም ባደረጉት ቁርጠኝነት ኩራት ይሰማናል። የሙዚቃ ዝግጅታቸው እንዴት እንደነበረ ለማየት በዚህ ዓመት መጨረሻ ከእነሱ ጋር ለመገናኘት በጉጉት እንጠብቃለን።

እርሶ በኢትዮጵያ የሚገኙ እና ሙዚቃን በሚሰጡት የህክምና እንክብካቤ አገልግሎት ላይ የመጠቀም ፍላጎት ያሎት ባለሙያ ኖት?

ኤረን እና ኤማ በገፈርሳ አእምሮ ጤና ህክምና ማዕከል፣ ፌናይድ፣ ሆስፒስ ኢትዮጵያ እና ለቤዛ የስነ አእምሮ ክሊኒክ ላሉ አጋሮቻችንን ለመጎብኘት በዚህ አመት ሊመለሱ ይችላሉ፡፡

ድንቅ ነበር፡፡ በዚህ መቀጠል አለባችሁ

በፌናይድ የሚገኙ አንድ ተሳታፊ ሰራተኛ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሆነ እና በአዕምሮ ጤና እንክብካቤ ላይ ሙዚቃን ስለመጠቀም የመማር ፍላጎት ካላችሁ የአለምአቀፍ ብሮግራም አስተባባሪያችንን ማክዳ ሚሼልንድጋፍ እንዴት እንደምናደርግላችሁ ለተጨማሪ መረጃ በኢሜል makedamitchell@musicastherapy.org ማነጋገር ትችላላችሁ፡፡