(Read this in English.)

በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው የሆስፒስ አገልግሎት ስር በሚገኘው የቀን እንክብካቤ ማዕከል ወስጥ ፍላጎት ታደለ እና ወንጌል ያሬድ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን ያካሄዳሉ። ፍላጎት ለአራት ዓመታት ያህል እንደ ሲኒየር ፓሊየቲቭ ነርስ ሆና የምታገለግል ስትሆን ወንጌል ደግሞ እንደ የፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ለሁለት ዓመታት ያህል በሆስፒስ ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች። የፍላጎት ኃላፊነቶች በየእለቱ እስከ 6 የሚደርሱ ታካሚዎችን በህመማቸው ክብደት አንፃር ማየት እና በመመርኮዝ ማስታገሻ ህክምና እና ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ድጋፍን ያጠቃልላሉ። ወንጌል የሆስፒስ ኢትዮጵያን ጠቅላላ ፕሮጄክቶች እና ስልጠናዎች ላይ የማቀድ፣ የማደራጀት እና ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነት አለባት።

ወንጌል እና ፍላጎት ከሙዚቃ ቴራፒስቶች ኤማ እና ኤሪን ሙዚቃን በህክምና መንገድ የመጠቀም መሰረታዊ መርሆችን በ2015 ከመማራቸው በፊት ምንም አይነት መደበኛ የሙዚቃ ስልጠና ዳራ እንዳልነበራቸው ይናገራሉ። ነገር ግን በሰፊው ማህበረሰባቸው በሙዚቃ ተከበው – የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ በመመልከት እና በመጨፈር ይሳተፉ እንደ ነበር ይናገራሉ።፡ፍላጎት በተለይ በልዩ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ እንደሚያስደስታት ትናገራለች። ፍላጎት የሆስፒስ ኢትዮጵያ ቡድንን ስትቀላቀል እና ሌሎች ነርሶች ከሙዚቃ ቴራፒስት ሃና እና ረዳቷ ሊሊ (2011) የተማሩትን የሙዚቃ ችሎታቸውን ሲያካፍሏት የራሷን የባህል ሙዚቃ ልምድ ወደ ስራዋ ማምጣት የተፈጥሮ እድገት እንደነበር ትናገራለች። 

ፍላጎት በአንድ ባልደረባዋ ሲመራ ያየችው የመጀመሪያው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ላይ ታካሚዎች አብረው በሙዚቃ ለመደሰት ሲሰበሰቡ ታስታውሳለች። ፍላጎት በቀደሙት የስራ ቦታዎቿ ላይ እንደዚህ አይነት የሙዚቃ እንቅስቃሴዎችን አይታ አታውቅም ነበር፣ ነገር ግን በሆስፒሱ ውስጥ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ለታካሚዎች እንዴት የተለያዩ እድሎችን እንደሚሰጡ ተመለከተች።

ወንጌል ለመጀመርያ ጊዜ ያየችው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ በፍላጎት የተመራ ሲሆን በቀን እንክብካቤ ማዕከል ወስጥ ሕሙማን እንደ ክበሮ ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን በመጠቀም የባህል ሙዚቃዎችን እየተጫወቱ ነበር። ወንጌል ሕመምተኞቹ በሙዚቃው ሲጨፍሩ እና በመሳተፋቸው ያሳዩትን ደስታ ስትመለከት ትዝ ይላታል።

ወንጌል በኤሪን እና በኤማ ለመጀመርያ ጊዜ ሲመራ የተመለከተችው ክፍለ ጊዜም ሌላ ትልቅ እና ጠቃሚ ክስተት እንደነበር ታስታውሳለች።

በዚያን ጊዜ በቋንቋ እንኳን ባይግባቡም ሙዚቃ ሁሉንም ሰው እንደሚያገናኝ መረዳት ችያለሁ። ኤሪን እና ኤማ ከሕሙማኑ ጋራ በአማርኛ መግባባት ባይችሉም ይዋደዱ ነበር። እኔ ባልገባኝ መንገድ ተግባብተው ነበር። በጣም አስደሳች እና ሞቅ ያለ ጊዜ ነበር። የተለያዩ ቴክኒኮችን አስተምረውን ነበር እናም እንዚህን ቴክኒኮች ከታካሚዎች ጋር እንለማመዳለን። ለመስራት ቀላል እና አስደሳች ነበር፣ ተፅእኖ እንዳለውም አይተናል።

ወንጌል

ፍላጎት በ2015 ከተሰጠው ስልጠና በፊት የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች የተቀረጹ የኢትዮጵያ ዘፈኖችን ማዳመጥ ወይም የሙዚቃ መሳሪያዎችን በመጠቀም ባህላዊ ሙዚቃን መጫወት በቻ ያካትቱ እንደነበር ትናገራለች። ኤሪን እና ኤማ የበለጠ ሳቢ እና ታካሚዎች በአንዳንድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ሊሆኑበት የሚያስችል የሙዚቃ አጠቃቀም መንገድ አሳይተዋቸዋል። ወንጌል እነዚህን የተለያዩ የሙዚቃ ቴክኒኮችን ከተማረች እና አንዳንድ ክፍለ ጊዜዎችን ካየች በኋላ የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜዋን መምራት ለእሷ አዲስ ነገር ስለነበር ትንሽ ከባድ እና አስቸጋሪ መስሎ እንደታያት ትናገራለች። ነገር ግን አስደሳች ስለነበር እየቀለለ እንደመጣ ተገንዝባለች። አሁን በየአመቱ ወደ 20 የሚጠጉ ታካሚዎች በማዕከሉ የሚዘጋጁት የቡድን ሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ይሳተፋሉ።

ወንጌል እና ፍላጎት በማዕከሉ ወስጥ ስለሚገኝ እና ከተለያዩ ከባድ ሕመሞች ጋር የሚኖር እንድ ታካሚ ይናገራሉ። ይህ ታካሚ የማዕከሉን አገልግሎት በማግኘቱ ደስተኛ እንደሆነ እና የሙዚቃ ዝግጅቶቹን፣ በተለይ ከበሮን መጫውት፣ እንደሚወድ ጠቅሷል። ታካሚው ከኤማ እና ከኤሪን ጋር ያነበረውን ጊዜ በጣም ወዶት ነበር፣ እና የሙዚቃ ቴራፒስቶቹንም ‘ልጄ’ በማለት ይጠራቸው ነበር።

ወንጌል እና ፍላጎት ከኤማ እና ኤሪን በተማሩበት መንገድ ክፍለ ጊዜን መምራት ሲጀምሩ አዳዲስ የሙዚቃ አይነቶችን በማካተታቸው ለታካሚው ትንሽ ግራ የመጋባት ነገር ነበር። ይሁን እንጂ ሙዚቃን የሚጠቀሙበት መንገድ ውስብስብ ስላልሆነ ታካሚው አዲስ ክፍለ ጊዜዎቹን በፍጥነት መልመድ ችልዋል። ለምሳሌ፣ ታካሚው የሙዚቃ እንቅስቃሴዎችን  ለመምራት ዓይናፋር ነበር፣ ነገር ግን አንድ ጊዜ እንዲመራ ካበረታቱት በኋላ መምራት ለታካሚው ከሚወዳቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተገኘ።

ወንጌል በሙዚቃ ክፍለ ጊዜው ውስጥ ስሳተፍ ታካሚው የበለጠ ደስተኛ መሆኑን እና በጥልቅ ሀሳብ ላይ የሚውልበት ጊዜ እየቀነሰ መሄዱን ተመልክታለች። ፍላጎት ክፍለ ጊዜዎቹ ስለታካሚው ማንነት የበለጠ እንድታውቅ ርድቷታል። የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ለታካሚው ከሚያስገኙት ጥቅሞች መካከል መደሰት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለውን ማህበራዊ ግንኙነት ማበረታታት እና ውጥረቶችን እና ግላዊ ጉዳዮችን ለመቋቋም ማስቻል ይቆጠራሉ።

ፍላጎት እና ወንጌል በሌሎች ታካሚዎች ተመሳሳይ መሻሻልን ተመልክተዋል እንዲሁም የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ሌሎች ታካሚዎች ስለ እራሳቸው ሲከፍቱ፣ በቡድን ሲሳተፉ እና ከሌሎች ጋር ሲገናኙ የሚያግዛቸው እንደሆነ አይተዋል።

የሙዚቃ ሕክምናው ከራሳቸው ጋር እንዲገናኙ ይረዳቸዋል። እኛ እንደ ህመም ማስታገሻ እንጠቀመዋለን። ከስቃያቸው እና ከስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸው የማዘናጊያ አንዱ መንገድ ነው። ከማስደሰትም ጭምር እነዚህን ጥቅሞች ይሰጣል።

ፍላጎት

ሌላ በከባድ በሽታ የተያዘ ህመምተኛ ከዚህ ቀደም የቀን ማዕከሉ በሚያዘጋጀው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ትዝናና ነበር። መጀመሪያ ላይ ይቺ ታካሚ በባህላዊ ሙዚቃ ማዳመጥ እና መደነስ ላይ ያተኮረ የድሮውን የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ አሰራር ትመርጥ ነበር። በአዲሱ አሰራር እንደ ኮንዳክቲንግ ያሉ ቴክኒኮች ላይ ለመሳተፍም ፍላጎት አልነበራትም። ነገር ግን ከኤማ እና ከኤሪን ስልጠና የመጡ አዳዲስ የሙዚቃ አጠቃቀሞችን ለመሞከር ቆይታ ተቀባይ ሆነች። ፍላጎት በሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ምክንያት ታካሚዋ ከሌሎች ጋር ስትገናኝ እና እራሷን በተሻለ ሁኔታ ስትገልጽ አይታለች። ታካሚዋ በማዕከሉ ውስጥ ካሏት ጓደኞች ጋር አብራ ስትሆን እና በሙዚቃ ስትዝናና የበለጠ ከማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳዮች የተገላገለች ትመስል ነበር።

ታካሚዋ በሆስፒሱ ወስጥ ካለው ማህበር ጋር ጠንካራ ግኑኝነት ይሰማት እንደ ነበር ግልፅ እየሆነ መጣ።ጎረቤቶቿ የት እንደምትሄድ ሲጠይቋት ሆስፒስ ኢትዮጵያ ያለኝን ቤተሰብ ለመጠይቅ ብላ እንደምትመልስላቸው እዛ ልሚገኙት ባለሙያዎች ትናገር ነበር።

የታካሚዎች የደስታ ስሜት እና ስለሙዚቃ ክፍለ ጊዜ የሚሰጡት አወንታዊ አስተያየት ለፍላጎት ሙዚቃን በሕክምና መንገድ መጠቀም ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ያረጋግጣሉ።ወንጌል ደግሞ ሙዚቃ የድቡን ግንኙነትን ስለሚጨምር አስፈላጊ ነው ብላ ታምናለች።

ታካሚዎች ፈገግ ብለው እና መሳሪያዎቹን ለመጠቀም ሲሞክሩ ማየት አስደሳች ነው። እንድንኮራ ያደርገናል።

ወንጌል

ሆስፒስ ኢትዮጵያ ለህፃናት የሆስፒስ አገልግሎት በመስጠት ወደፊት አገልግሎቱን እንደሚያሰፋ ተስፋ ያደርጋል። ወንጌል እና ፍላጎት ልጆችን እንዴት በክፍለ ጊዜ ወስጥ ማካታት እንደሚችሉ እርግጠኛ ባይሆኑም፣ ሙዚቃ በልጆች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ። ሙዚቃ ልጆችን ከአካላዊ ህመማቸው ለማዘናጋት ውጤታማ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ይገነዘባሉ። ፍላጎት እና ወንጌል ልጆች ከአዋቂ እና አዛውንት ይልቅ የሙዚቃ ቴክኒኮችን ማላመድ ይቀላል ብለው ያስባሉ። ልጆችም እንደ አዋቂ የሚሰሙትን ሙዚቃ አይነት ብዙ አያማርጡም ብለው ያስባሉ።

ሆስፒስ ኢትዮጵያ የቤት ውስጥ እንክብካቤን በሚሰጥበት ጊዜ ሙዚቃን መጠቀም እንዲጀምር ፍላጎት አለ፣ ነገር ግን ፍላጎት ሙዚቃን በቤት ውስጥ ለመጠቅም በመጀመርያ በጥንቃቄ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ተረድታለች።