በ ገፈርሳ የአዕምሮ ጤና እና የማገገሚያ ማዕከል በሙዚቃ ግንኙነትን መፍጠር
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Mental health
ቡላ ኤታና የኢትዮጵያ አካል ጉዳት አገልግሎት ስር በሚገኘውን ገፈርሳ የአዕምሮ ጤና እና የማገገሚያ ማዕከል ውስጥ የነርስ እና ጥራት ኦፊሰር ሆኖ ያገለግላል።የቡላ የነርሲንግ ኃላፊነቶች ታካሚዎችን መንከባከብ ሲያካትቱ፣ እንደ ጥራት ኦፊሰር ደግሞ ኃላፊነቱ ለተሃድሶ ማእከል ፕሮቶኮሎችን እና መደበኛ ሂደቶችን መፍጠር፣የተወሰኑ የሕክምና ዘዴዎችን (እንደ ሙዚቃ እና አርት ቴራፒ ያሉ) ማዳበር እና ማሳደግን ያካትታል።ቡላ በማዕከሉ ለ9 ዓመታት ሲሰራ የቆየ ሲሆን ማዕከሉን ለታካሚዎች ምቹ ለማድረግ ቆርጧል። ቡላ የሙዚቃ ዳራ ስላለው ጊታር እና ኪቦርድ በመጫወት የራሱን ዘፈኖች ይፈጥራል።
ቡላ በ2011 የሙዚቃ ቴራፒስት ሃና ብርሃኑ እና ሊሊ ብሎውስ-ፓሊዎዳ በሰጡት የሙዚቃ ስልጠና ላይ ተሳትፎ ነበር። ከተሳታፊዎችም በማዕከሉ እየሰራ ያለው ብቸኛው የሰራተኛ አባል ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን አልፎ አልፎ በመምራት እና በመርዳት ላይ ይገኛል። በ 2015 ተጨማሪ ባልደረቦች በሙዚቃ ቴራፒስቶች ኤሪን ዊሊያምስ-ጆንስ እና ኤማ ብሪትተን ሙዚቃን እንዲጠቀሙ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። አሁን የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች በየሳምንቱ ሐሙስ ቀን ላይ ይዘጋጃሉ። ሆኖም ቡላ በሳምንት አንድ ጊዜ በቂ እንዳልሆነ እና የሙዚቃ ዝግጅቶች በሳምንት ሁለት ጊዜ ቢደረጉ የየተሻለ እንደሚሆን ይሰማዋል።
ቡላ የመጀመርያውን የሙዚቃ ስልጠናውን ሲያሰላስል ሃና እና ሊሊ ሲመሩ ባየው የመጀመሪያ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ በተለይ አዲስ ነገር በመሆኑ መገረሙን ያስታውሳል። ሃና ያካፈለችው መረጃ አስደሳች እንደነበርም ያስታውሳል። ሙዚቃን በግለሰብ ክፍለ ጊዜዎች መጠቀምን ተምሯል እና ብዙ ጊዜ ሙዚቃ የታካሚዎችን ትዝታ እንዴት እንደሚያነሳ እና ከዚህ በፊት ስለ ግል ልምዳቸው እንዲናገሩ እንደሚፈቅድላቸው ተመልክቷል።
ከሙዚቃ ቴራፒስት የ1 ለ 1 የስርዓትን ነው የተማርኩት። ይህን ከአንድ ታካሚ ጋር ስጠቀም በዛ ሙዚቃ ዘፈን መዝፈን ጀመረ። የቀድሞ ታሪኩን አስታወሰ። ትዝታውን መዝፈን ጀመረ። ይህንን አስታውሳለሁ። ያንን ሙዚቃ ለምን እንደ መረጠ ስጠይቀው፣ በዛ ዘፈን የሚያስታውሰውን ታሪክ ነገረኝ።
ቡላ የመጀመሪያ የመራውን የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ያስታውሳል፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠውን ታካሚ ወደ ክፍለ-ጊዜው ለመሳብ እና በሙዚቃ እንቅስቃሴዎች ለመምራት ምን ያህል ከባድ እንደ ነበር ይናገራል። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ክፍለ ጊዜዎችን መምራት ለቡላ ቀላል እየሆነ ሄዷል።
ቡላ ታካሚዎች የሙዚቃ መሳሪያዎችን ሲጫወቱ እና የህይወት ታሪካቸውን ሲናገሩ ኩራት ይሰማዋል (ለዚህም ነው ከትላልቅ የቡድን ክፍለ ጊዜዎች ይልቅ የነጠላ ክፍለ ጊዜዎችን የሚመርጠው)። ቡላ የግለሰብ ክፍለ ጊዜዎች ለታካሚዎች ስሜታቸውን እንዲገልጹ እና ከእሱ ጋር የበለጠ እንዲገናኙ የበለጠ እድል ይሰጣሉ ብሎ ያምናል። በንፅፅር በቡድን ክፍለ ጊዜዎች ትኩረቱ ይበልጥ በመዝናናት ላይ ስለሚሆን ከታካሚዎች ጋር የላቀ ግንኙነትን ለመገንባት ከባድ እንደሚያደርገው ቡላ ተመልክትዋል።ቡላ በቅርቡ የግል የሙዚቃ ክፍለ ጊዜውን እንደገና ጀምሯል እና ባልደረቦቾቹም ምሳሌውን ትከትለው ከታካሚዎች ጋር ሙዚቃን በነጠላ ክፍለ ጊዜ ሲመሩ ማየት ይፈልጋል።
በአሁኑ ወቅት 30 የሚሆኑ ታካሚዎች በማዕከሉ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ይሳተፋሉ።ቡላም ለታካሚዎች የሚሰጠውን ጥቅም ማየት ችሏል። ከታካሚዎቹ አንዱ በማዕከሉ ውስጥ ከ 5 ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን በብዙ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችም ተሳትፏል።
ለሱ አላማ አለኝ። የሙዚቃ ህክምና ለእሱ በጣም ጥሩ እንደሆነ አውቃለሁ… ሰዎች ስሜታቸውን የሚገልጹት በሙዚቃ ነው። ሲዘፍኑ ነጻ ናቸው።
ይህ ታካሚ ስኪዞፈሪንያ ያለበት ሲሆን በህመሙ ምክንያት በጣም እረፍት አልባ ሊሆን ይችላል፣ አንዳንድ ጊዜም በንግግር ላይ አስተሳሰቡ ይምታታበታል፣ ግን የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች እድገት እንዲያደርግ እና እንዲሻሻል ረድተውታል፥
በመጀመሪያዎቹ ቀናት ለመሳተፍ ሽልማት ያስፈልገው ነበር፣ አሁን ግን ይህ ቀርቷል። ሲጠራ መጥቶ መሳተፍ ጀምሯል። አሁን እንደ መዝናናት እያየው ነው። የሙዚቃ ቴራፒ የሚኖር ከሆነ እራሱ እየጠየቀ ነው።
ቡላ ከሌሎች ታካሚዎች ጋር ተመሳሳይ መሻሻልን ተመልክቷል። ታካሚዎች በፈቃደኝነት በክፍለ ጊዜዎች እየተሳተፉ እና እየተደሰቱ ነው። በነጻነት ሃሳባቸውን እየገለጹ እና የህይወት ልምዳቸውን እያወሩ ነው፣ይህም ከሌሎች ጋር እንዲገናኙ እና ከአእምሮ ህመማቸው አንፃር አወንታዊ ጥቅም እንዲያገኙ እየረዳቸው ነው።
ቡላ ሙዚቃ ለህክምና ጠቃሚ እና አስፈላጊ ነው ብሎ ያስባል። እንደ ማንኛውም ሰው ሙዚቃ ለታካሚዎች ሀሳባቸውን ለመግለጽ እና ንቁነታቸውን ለማሻሻል እንደ ሚረዳቸው ተገንዝቧል።
ቡላ ገፈርሳ የአዕምሮ ጤና እና የማገገሚያ ማዕከል ከሙዚቃ፣ ከሙዚቃ ቴራፒስቶች እና ከMusic as Therapy International እየተደረገ ባለው ድጋፍ ተጠቃሚ መሆኑን ተመልክቷል። ማዕከሉም ከቀጠለባቸው ተግባራት መካከል የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች አንዱ ነው። ነገር ግን ስለ ሙዚቃ ሕክምና የተማረው በቂ መሆኑን ወይም ተጨማሪ የሚማረው ነገር ካለ ቡላ ይጠይቃል። ቡላ በነርስነት ሙያው ለዓመታት የሰለጠነበት ሲሆን፣ ለሙዚቃ ህክምና የአንድ ወር ሥልጠና አጭር ሆኖ እንደሚታየው ተናግሯል። ሙዚቃን ለህክምና መጠቀም ብቃት እንዳለው የሚያሳዩ የዲግሪ ወይም የዲፕሎማ መመዘኛዎች እና የምስክር ወረቀቶችን ማግኘት የሚቻል ከሆነም ቡላ ማወቅ ይፈልጋል።
Related projects
-
Partner Newsletter: Ethiopia 2024
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Disability
- Elderly
- Mental health
- Young people