FENAID የመማር እክል ላለባቸው ግለሰቦች ሙዚቃን እንዴት ለማበረታቻ እንደሚጠቀም
Ethiopia
- Caregivers
- Disability
- Young people
- Unpaid carers
የፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር የራስ ተሟጋች መሪ ኪሩቤል አንተነህ እና እናቱ ብርቱካን የሱፍ በ2015 በሙዚቃ ቴራፒስቶች ኤማ ብሪትተን እና ኤሪን ዊሊያምስ-ጆንስ በተሰጠው የሙዚቃ ስልጠና ላይ ተሳትፈው ነበር።በፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ስር እንደ መሪ ከማገልገልንም አልፎ ወጣቱ ኪሩቤል የመማር ውስንነት ጋር ቢኖርም ብዙ ፍላጎት ያለው ሰው ነው። ኪሩቤል የማዕከሉን አገልግሎት ከስድስት እስከ ሰባት ዓመታት ያህል ሲጠቀም ቆይቷል።
እኔ የአዕምሮ ጉድለት ያለበት ሰው መሆኔን ሰዎች እንዲያውቁ እፈልጋለሁ ነገር ግን ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ፤ እና የአዕምሮ ጉዳተኞች እድል ከተሰጣቸው ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ለሰዎች ማሳወቅ እፈልጋለሁ።
ኪሩቤል
እንደ ራስ ተሟጋች መሪ የኪሩቤል ኃላፊነቶች በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች ግለሰቦች እንደ አካል ጉዳተኛ ስለመብታቸው እና ለመብታቸው መቆም እንዴት እንደሚችሉ ማስረዳት እና መግለጽን ያካትታሉ። ኪሩቤል ከእኩዮቹ መካከል በየቀኑ ማን እንደሚገኝ እና ማን እንደሚቀር ይከታተላል። ኪሩቤል ከሌሎች የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስላለው እነሱ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ለማዕከሉ አስተዳደር እየለየ ያስተላልፋል። ኪሩቤል ፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበርን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶችን በራሱ የቲክቶክ አካውንት ያስተዋውቃል።
የኪሩቤል የዕለት ተዕለት ተግባር በፍቅር ኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበርን በተለምዶ በጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም ከእኩዮቹ ጋር ስፖርት በመጫወት የሚጀምር ሲሆን ከዚያም ኪሩቤል ሌሎችን ወደ ቀጣዩ ክፍል በመምራት ይረዳል። ከምሳ በኋላ ኪሩቤል ከተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን (United Nations Convention on the Rights of Persons with Disabilities (UNCRPD)) እኩዮቹን ስለመብታቸው የሚያስተምር አንቀጽ ይመርጣል። በኋላ ላይ ኪሩቤል በቲኪ ቶክ ቪዲዮዎች ላይ ሊሰራ ይችላል።
ኪሩቤል እንደ ራፕ ሙዚቃ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሉ ብዙ ፍላጎቶች አሉት። ኪሩቤል በፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር በስፖርት እና የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ መሳተፍ ይወዳል፣ የወንድ ጓደኞቹን ከማዕከሉ አስተዳደር ጋር በሚደረጉ ስብሰባዎች በመወከልም ይደሰታል። ኪሩቤል ለሙዚቃ ያለው ፍቅር እና በፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር የሚገኘውን የሙዚቃ መሣሪያ መጠቀም መቻሉ በ2015 በተሰጠው የሙዚቃ ሥልጠና ተሳትፎ እንዲደሰት አድርገውታል።
የሙዚቃ ስልጠናው ኪሩቤል የተለያዩ የሙዚቃ ዜማዎችን እና የኢትዮጵያን የሙዚቃ ዘውጎችን (እንደ ተዘታ፣ ባቲ፣ አምባሰል እና አንቺሆይ) በመለየት እና ከሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ባለፈ በሙዚቃ ምርጫ ላይ የበለጠ እንዲያተኩር በማድረግ ረድቶታል።
የመጀመሪያው ነገር ኪሩቤል የእግዚአብሔር በረከት ነው። በፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር በሚያደርገው ነገር ሁሉ እኮራለሁ። የአእምሮ እክል ያለባቸው ሰዎች እድሎች እስካገኙ ድረስ ወይም ስልጠና እስካገኙ ድረስ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ምሳሌ ነው።
ብርቱካን
Bብርቱካን ስለ ሙዚቃ አጠቃቀም እና ሙዚቃ ለአካል ጉዳተኞች እንዴት ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ብዙ ስለተማረች በሙዚቃው ስልጠና ላይ መሳተፍ አስደስቷታል። እንደ እናት ለእሷ ትልቅ እና ጠቃሚ እድል እንደነበር ነገረችን።
ኪሩቤል እና ብርቱካን በኤሪን እና በኤማ የሚመራውን የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ ሲያዩ ደስተኛ እንደነበሩ ያስታውሳሉ፣ምክንያቱም ኪሩቤል ሙዚቃን ስለመጠቀም ለመማር በእውነት ፈልጎ ነበር። ብርቱካን የሙዚቃ ቴራፒስቶች አገልግሎቱን በማቅረባቸውም ተደስታ ነበር። በመጀመሪያዎቹ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች በርቱካን እና ኪሩቤል እራሳቸውን ይመሩ ነበር፣ በሙዚቃ መሳሪያዎች ድምጽ በማሰማት፣ ሪትሞችን በመፍጠር እና የሙዚቃ እንቅስቃሴዎችን እንዴት መጀመር እና ማቆም እንደሚችሉ ይማሩ እንደነበር ያስታውሳሉ። ብርቱካን በቡድን ክፍለ ጊዜዎች ውስጥ ትርጉም ያለው ድምጽ ማሰማት እንደምትችል ተሰምቷት ነበር፣ እና እንደዚህ አይነት ስልጠና እና የሙዚቃ መሳሪያዎች ለአካል ጉዳተኞችን እንደሚጠቅሟቸው እና እንደሚያበረታቷቸው ተገንዝባ ነበር።
ይህ የሙዚቃ ህክምና ለልጆቻችን በጣም አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ያነሳሳቸዋል እና ንቁ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። የዚህ አይነት ክፍለ ጊዜ እና መሳሪያዎቹ እስካላቸው ድረስ በጣም ሊበረታቱ ይችላሉ።
ብርቱካን
ኪሩቤል በሙዚቃ ድምጾች እየተዝናና በፍቅር ኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር የሚዘጋጁ የሙዚቃ ዝግጅቶች መደሰቱን ቀጥሏል። ክፍለ-ጊዜዎቹ ኪሩቤል እና ሌሎች አካል ጉዳተኞች ሀሳባቸውን በሙዚቃ ሲገልጹ እና ሪትሞችን እንዲለዩ እና ስለ ሙዚቃ በዝርዝር እንዲያውቁ ረድተዋቸዋል።ኪሩቤልም የራሱን ሙዚቃ ለመፍጠር በክፍለ-ጊዜዎች ተነሳስቶ ነበር። ስለዚህ ከሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ባሻገር ኪሩቤል ፒያኖን በማግኘቱም ተደስቷል። ብርቱካን የኪሩቤልን የሙዚቃ ፍላጎት እና መሳሪያዎችን ለማሰስ ድፍረት ሲያድግ አይታለች።
የሙዚቃ ዝግጅቶቹ ኪሩቤል ከፍቅር ኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር የሚገኙትን ጓደኞቹ ጋር እንዲቀራረቡ ረድተውታል። አዳዲስ ተሳታፊዎችም ሲመጡ ኪሩቤል እንዲሳተፉ ያበረታታል፣ ከነሱም መማር የፈልጋል።
ብርቱካን በፍቅር ኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ቀኗን ማሳለፍ ስለማትችል ከሥልጠናው ጊዜ ጀምሮ የክፍለ ጊዜን አልመራችም። ነገር ግን ብርቱካን እና ኪሩቤል በቤት ውስጥ ሆነው ሙዚቃን በአንድ ላይ ተጠቅመዋል። ሁለቱም ሙዚቃ ስለሚወዱ አንዳንድ ጊዜ ሙዚቃ እያጫወቱ አብረው ይጨፍራሉ።
አዎ፣ ሙዚቃው በደንብ እንድንተዋወቅ ረድቶናል። ኪሩቤል ስለሚያውቀው ስለተለያዩ ሪትሞች እና ስለመሳሰሉት ያስተምረኛል; “እማዬ ይሄ ነው ይሄ ነው” ይላል።
ብርቱካን
እንደ እናት፣ ብርቱካን አካል ጉዳተኛ ልጆች ላሏቸው ወላጆች ድጋፍ እንደሚያንስ ተገንዝባለች።ወላጆች ሙዚቃን በሕክምና መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የበለጠ እንዲማሩ ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚገባ ታምናለች። ብርቱካን ሌሎች እናቶች ሙዚቃ ለልጆቻቸው ጉዞ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እና ልጆቻቸውን እንዲነቃቁ እንደሚረዳቸው እንዲያውቁ ትፈልጋለች።
Related projects
-
Partner Newsletter: Ethiopia 2024
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Disability
- Elderly
- Mental health
- Young people