በ ለቤዛ የስነ ዐዕምሮ ክሊኒክ ለአእምሮ ጤና ታካሚዎች የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ የፈጠረው ጥላ
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Mental health

የሙዚቃ ቴራፒስቶች ኤሪን እና ኤማ በለቤዛ የስነ አዕምሮ ልዪ ክሊኒክ የሙዚቃ ስልጠና በ2015 ተሰጥቷል። በስልጠናው እየሩሳሌም አለማየሁ እና ብስራት ቤኛ የተሳተፉ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጌትነት አሰፋ አብረው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። እየሩሳሌም በክሊኒኩ ለሰባት ዓመታት ያህል እየሰራች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ምክትል ዋና ክሊኒካል ኦፊሰር ናት። ለ41 ዓመታት በአእምሮ ህክምና ያገለገሉት ብስራት ከ8 ዓመታት በፊት ለቤዛ የስነ አዕምሮ ልዪ ክሊኒክ ቡድንን ከመቀላቀላቸው በፊት በገፈርሳ የአዕምሮ ጤና እና የማገገሚያ ማዕከል ይሰሩ ነበር። አሁን ለቤዛ የስነ አዕምሮ ልዪ ክሊኒክ ወስጥ እንደ እና ዋና ነርስ ያገለግላሉ። ጌትነት በክሊኒኩ በአስተዳዳሪነት ለአንድ ዓመት ተኩል ሲሰራ ቆይቷል።
እየሩሳሌም ክሊኒኩ ለተቀማጭ እና ለተመላላሽ ታካሚ ለሚሰጠው ወቅታዊ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ኃላፊነት አላት። የሳይኪያትሪ ነርሶችንም ትቆጣጠራለች። እየሩሳሌም ገፈርሳ የአዕምሮ ጤና እና የማገገሚያ ማዕከል ሙዚቃን ለህክምና እንደሚጠቀም ከባልደረባዋ ከተረዳች በኋላ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን ወደ ለቤዛ የስነ አዕምሮ ልዪ ክሊኒክ ማምጣት ፈለገች። ቀጥሎም የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች እንደ መጽሐፍ ክበብ፣ የሙያ ቴራፒ፣ እና የግለሰብ እና የቡድን ቴራፒ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ጎን ለታካሚዎች እንዲቀርቡ ተወሰነ።
ለታካሚዎቻችን ለማቅረብ የተለያዩ ተግባሮችን እየተመለከትን ነበር። እንደ የቤት ውስጥ ጨዋታዎች የመሳሰሉ ነገሮች እንዲቀርቡላቸው ታካሚዎች ብዙ ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ሙዚቃን ለታካሚዎቻችን እንደ ሕክምና መጠቀም መቻላችን ጥሩ አጋጣሚ ነበር። የመጣበት ጊዜው ለእኛም በጣም ጥሩ ነበር። የተለያዩ ነገሮች ላማቅረብ እየሞከርን ነበር ግን በጣም ከባድ ነበር። የተለያዩ የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን በንሞክርም ታማሚዎቹ ይሰለቻቸው ነበር።
እየሩሳሌም
ብስራት የክሊኒኩ ዋና ነርስ በመሆናቸው ብዙ ኃላፊነቶች አሉባቸው። እነዚህም ከሀኪሞች ጋር ስለ ታማሚዎች ውይይት ማድረግ፣ የታካሚዎችን መሻሻል መከታተል፣ የታካሚ ቤተሰቦችን ማነጋገር እና ሌሎች ነርሶችን መቆጣጠርን ያካትታሉ።
የጌትነት ሚጫወተው ሚና የታካሚዎችን ፍላጎት ማሟላት፣ ለምሳሌ የመድሃኒት አስተዳደር እና የታካሚዎችን የግል ንፅህና መከታተልን አይነት ስራዎችን ያካትታል።ጌትነት ለታካሚዎች በጣም ተንከባካቢ እና ጠቃሚ የክሊኒኩ የስራ አባል ሆኖ ይታያል።
የታካሚዎች ክፍል 35 አልጋዎች ያሉት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ አልጋዎቹ እንደተያዙ ናቸው። ታማሚዎች እንደ በሽታቸው እና መሻሻላቸው በክሊኒኩ ውስጥ ለጥቂት ሳምንታት ወይም እስከ 3 ወራት ሊቆዩ ይችላሉ። በ2015 ስልጠናውን ከመውሰዱ በፊት ክሊኒኩ ሙዚቃን እንደ ህክምና ተጠቅሞ አያውቅም ነበር። ሰራተኞቹም ከሙዚቃ እና የሙዚቃ መሳሪያ ጋር ልምድ አልነበራቸውም።አሁን፣ በክሊኒኩ በሚቆዩበት ጊዜ፣ ታካሚዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ፣ በየሰኞ እና አርብ ከሰአት በኋላ፣ በሙዚቃ ክፍለ ጊዜ መሳተፍ ይችላሉ።
ከመጀመሪያ ስልጠናቸው ጊዜ ቢያልፉም እየሩሳሌም ከሙዚቃ ቴራፒስቶች የተማረቻቸውን ነገሮች ታስታውሳለች። ስልጠናው እየሩሳሌምን ከዚህ በፊት አይታ የማታውቃቸውን በርካታ የሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር አስተዋውቋታል። ታካሚዎችም ሙዚቃን በለመዱበት ፍጥነት የለምዳሉ ብላም አልገመተችም ነበር።
ኢየሩሳሌም በመራችው የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ‘ጥሪ እና ምላሽ’ ብሎ የሚጠራ ተግባርን አካታለች። ኢየሩሳሌም ተግባሩን መምራት ጥሩ ተሞክሮ እንደነበር ብታስታውስም ታማሚዎች የ ‘ጥሪ እና ምላሽ’ ዘዴን ለመከተል እንደተቸገሩ ትናገራለች። የኤማ እና ኤሪን እርዳታ ግን ርድቷታል ብላለች።
ብስራት የኤሪን እና ኤማ ንየመጀመሪያ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ለክሊኒኩ አዲስ ነገር በመሆኑ በታማሚዎች በኩል ምን አይነት አቀባበል እንደሚኖረው እርግጠኛ አልነበሩም። ብስራት ሙዚቃ የአንዳንድ ታካሚዎችን ህመም ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተመልክተዋል። በተለይም ባይፖላር ህሙማን በሙዚቃ ምክኒያት የበለጠ ሃይፐር እና ማኒክ ሊሆኑ እንደሚችህሉ ተገንዝበዋል። ነገር ግን ክፍለ ጊዜዎች በተደጋጋሚ ሲዘጋጁ እና ፈታኝ ባህሪያትን ለመቋቋም ሙዚቃን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የተሻለ ግንዛቤ በነበረ ጊዜ ዶ/ር ቢራስት በክፍለ-ጊዜዎቹ ላይ የበለጠ የመተማመን ስሜት ይሰማቸው ጀመረ።
ብስራት በስልጠናው ላይ የተሳተፉበት ዋና ምክንያት ስለ ሙዚቃ አጠቃቀም እውቀት በመቅሰም በሌሎች ነርሶች የሚመሩ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎችን ለመቆጣጠር ነበር። ስለዚህ በስልጠናው ወቅት ክፍለ ጊዜን ከመምራት ይልቅ ሙዚቃ በታካሚዎች ላይ ስላለው ተጽእኖ የበለጠ ለማወቅ በመመልከት እና በጥናት ነበር የተሳተፉት።በተለይም ሙዚቃ በታካሚዎች ስሜት ላይ ያለውን ተፅእኖ ለመመልከት ፍላጎት ነበራቸው። ብስራት ከታካሚዎች መድሃኒት ጋር በተያያዘ ሙዚቃ ተጽእኖዎች ካሉት፣ ታካሚዎች እርስ በርስ የሚግባቡ ከሆነ እና ታካሚዎች በክፍለ-ጊዜዎች ለመሳተፍ ፈቃደኝነታቸውን ነበር የሚመለከቱት።
ጌትነት በኤሪን እና በኤማ በቀጥታ የሰለጠነ ባይሆኑም ባለደረባው ሲመራው ያየውን የመጀመሪያ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ያስታውሳል። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ጌትነት በራሱ የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ መርቶ ህሙማኑ በሙዚቃ መሳሪያዎቹ እና እሱ በመምራቱ ሲደሰቱ ማየቱን ያስታውሳል። ይህም ለእሱ አስደሳች ጊዜ ነበር። ጌትነት የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ለታካሚዎች የመሰባሰብ እና የመደማመጥ እድል እንደሚሰጡ ይገነዘባል።
ቡድኑ እንደነገረን በክሊኒኩ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ይሳተፋሉ፣ ጥቂት ሰዎች ግን በሃይማኖታዊ ወይም በአእምሮአዊ ሁኔታ ምክንያቶች አይሳተፉም። አንዳንድ ጊዜ፣ አዲስ የገቡ ሕመምተኞች በሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ለመሳተፍ ዓይናፋር ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን አንዳንዶች ለመሳተፍ ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ሌሎች ወዲያው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ አሉ። ብስራት ባይፖላር ታማሚዎች በፈቃደኝነት በሙዚቃ ክፍለ ጊዜ እንደሚሳተፉ ተገንዝበዋል። ለባይፖላር ታማሚዎች ሙዚቃ ባህሪያቸውን የበለጠ ከባድ ሊያደርገውም ቢችል መሳሪያዎቹን በመጫወት ስለሚዝናኑ ስለራሳቸው ለመናገር ክፍት በመሆናቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ታካሚዎች የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ መጀመር ያለበትን ሳዓት ለሰራተኞች ያስታውሳሉ! ጌትነት ሌሎች ታካሚዎች በሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ምክንያት እንዴት የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነት እንደሚጀምሩ እና የበለጠ ምላሽ እንደሚሰጡ ተመልክቷል። የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ጌትነት ታማሚዎችን የተሻለ እንዲከታተል እና በደንብ እንዲተዋወቅ አስችሎታል።
ዲፕሬሽን ላላቸው ሰዎች፣ ለስኪዞፈሪንያ ታማሚዎች…[የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች] በተለይም መግባባት ለመፍጠር በጣም ጠቃሚ ነበሩ። ሙዚቃ ከሌሎች ጋር አነቃቂ ግንኙነት ሊሰጥ ይችላል።
ብስራት
በክሊኒኩ ሰራተኞች የሚከናወኑት የሙዚቃ ስራ ዓይነቶች ኤማ እና ኤሪን ካስተዋወቋቸው ጋር በጣም ተመሳሳይ ናቸው። የዶክተር ብስራት ማበረታቻም አሰልቺ እንዳይሆኑ ይረዳል።ቡድኑ ስል 1-ለ-1 የሙዚቃ ክፍለ ጊዜዎች ምማር ይፈልጋል። ለተመላላሽ ታካሚም እነዚህን አገልግሎቶች እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት አላቸው።
እየሩሳሌም፣ጌትነት እና ብስራት ክሊኒኩ በሚያዘጋጃቸው የሙዚቃ ዝግጅቶች እንዴት እንደሚኮሩ ተናግረዋል ። ክፍለ-ጊዜዎችን በሳምንት ሁለት ጊዜ ከአንድ አመት በላይ ማቆየት መቻላቸው አስደናቂ ነው። ቡድኑ በተጨማሪም አዳዲስ ግንኙነቶች ሲፈጠሩ እና በበሽተኞች መካከል ጓደኝነት ሲፈጠር ኩራት ይሰማቸዋል። ሙዚቃን ለህክምና መጠቀም እነዚህን ጥቅሞች ስለሚያበጅ ለለቤዛ የስነ አዕምሮ ልዪ ክሊኒክ አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባሉ።
ለታካሚዎቻችን የሚበጀው ከምንም ነገር በላይ ነው። ስለዚህ በታካሚዎቻችን ላይ ጉልህ የሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ አለ እና ይህን በሌሎች ድርጅቶች ላይ ማየት እፈልጋለሁ። ማንኛውም የስነ-አእምሮ ህክምና ተቋም ይህን መሰረታዊ የህክምና ዘዴ እንዲያካትት እመክራለሁ።
እየሩሳሌም
Related projects
-
Partner Newsletter: Ethiopia 2024
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Disability
- Elderly
- Mental health
- Young people